top of page

ATHEJIM

 

The author 3rd book “Athejim” is a collection of Short stories. By now Emebet’s talent to tell a story has expanded in elegance and prose, add that to her time growing up during the turbulent times of her beloved country, the outcome is “Athejim”, a powerful collection of short stories speaking about a time of sordid calamity mixed with love and longing. This book is her way of telling what happened to that generation. Just conjure the word Athejim in your mind and the possible circumstances surrounding it - it is a female going away, maybe a daughter to parents who do not wish letting their kid leave them, but had to, maybe a young man in love unwilling to separate himself from his first love, but had to, who knows!…Attend the book signing, meet Emebet, talk to her, get the book.   

እንቢ

 

እንቢ፣ እንቢ፣ እኔ አልናገርም፣

ለውጥ ላያመጣ ድምፄን አላውስም፤

ስተት ለማይገባው ለሌለው ህሊና፣

የርማት ግሰፃ ወቀሳ ነውና።

እናንተው ፍረዱ እኔ ልቅርባችሁ፣

ዝምታም ድምፅ ነው ድንገት ከገባችሁ።

ህሊና

 

ተጣልቼ ከራሴ፣

ሸንጎ መቆም ሆኖ ምሴ፣

ቀኑን ውዬ ስሟገት፣

የአእምሮ ሸንጎ ከሚሉት፣

የሀሳብ ትርምስ ካለበት፣

ወንጃይ ተወንጃይም፣ እኔው ሆኜ ዳኛ፣

ስሞግተው ውዬ ህሊና እንዳይተኛ፣

ግብ ግብ ገጥሜ ማስተዋል ከሚሉት፣

ድል አድርጌ መጣሁ እኔን አሸነፍኩት።

እጅ እና እግር

 

አንድ ግራ አንድ ቀኝ ሆኖ ፍጥረታቸው፣

አንዱ የቀረበውን ሌላው እየሸሸው፣

መራመድ ሲፈልግ አንደኛው ወደፊት፣

ወደ ሁዋላ ቀርቶ ሌላኛው ሲጎትት፣

አንዳንዴ ተስማምተው አንዳንዴ ሲጣሉ፣

እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ትግል ሲታገሉ፣

ቆርጬ አልጥላቸው ሆነውብኝ ገላ፣

ያስጠጉትን ስወድ የጠሉትን ስጠላ፣

ወደፊት አልሄድኩም ወይም ወደሁዋላ፤

  አሰታራቂ ሆኜ ለማያውቅ ልዩነት፣

ግራ አጋብቶኝ ቀረ ግራና ቀኝ ፍጥረት።

MY BOOKS
bottom of page